Isaiah 11

ከእሴይ ግንድ የወጣ ቍጥቋጥ

1ከእሴይ ግንድ ቍጥቋጥ ይወጣል፤
ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል።
2 የእግዚአብሔር መንፈስ፣
የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣
የምክርና የኀይል መንፈስ፣
የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
3 እግዚአብሔርን በመፍራት ደስ ይለዋል፤

ዐይኑ እንዳየ አይፈርድም፤
ጆሮውም እንደ ሰማ አይበይንም።
4ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤
ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤
በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤
በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
5ጽድቅ የወገቡ መታጠቂያ፣
ታማኝነትም የጐኑ መቀነት ይሆናል።

6ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይኖራል፤
ነብርም ከፍየል ግልገል ጋር ይተኛል፤
ጥጃ፣ የአንበሳ ደቦልና የሠባ ከብት
ዕብራይስጡ ከዚህ ጋር ይስማማል፤ የሰብዓ ሊቃናት ትርጕም ግን፣ የሠባ አንበሳ ይበላል ይላል።
በአንድነት ይሰማራሉ፤
ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል።
7ላምና ድብ በአንድነት ይሰማራሉ፤
ልጆቻቸውም አብረው ይተኛሉ፤
አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል።
8ጡት የሚጠባ ሕፃን በአደገኛ እባብ ጕድጓድ ላይ ይጫወታል፤
ጡት የጣለም ሕፃን እጁን በእፉኝት ጕድጓድ ይከትታል።
9በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ
ጕዳት ወይም ጥፋት አያደርሱም፤
ውሃ ባሕርን እንደሚሸፍን፣
ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።
10በዚያን ቀን፣ የእሴይ ሥር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ መንግሥታት ወደ እርሱ ይመጣሉ፤ ማረፊያውም የከበረ ይሆናል። 11በዚያን ቀን፣ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደ ገና የተረፈውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦር፣ ከታችኛው ግብፅ፣ ከላይኛው ግብፅ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኤላም፣ ከባቢሎን፣ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።

12ለመንግሥታት ምልክትን ያቆማል፤
ከእስራኤልም የተሰደዱትን መልሶ ያመጣቸዋል፤
የተበተኑትን የይሁዳ ሕዝብ፣
ከአራቱ የምድር ማእዘን ይሰበስባል።
13የኤፍሬም ምቀኝነት ያከትማል፤
የይሁዳ ጠላቶችም
ወይም፣ ባላንጣዎቹ
ይቈረጣሉ፤
ኤፍሬም በይሁዳ አይቀናም፤
ይሁዳም ኤፍሬምን አይጠላም።
14በምዕራብ በኩል በፍልስጥኤም ተረተር ላይ ይወርዳሉ፤
ሁለቱም ተባብረው በምሥራቅ ያለውን ሕዝብ ይዘርፋሉ፤
በኤዶምና በሞዓብ ላይ እጃቸውን ያነሣሉ፤
አሞናውያንም ይገዙላቸዋል።
15 እግዚአብሔር በሚጋረፍም ነፋስ፣
የግብፅን ባሕረ ሰላጤ ያደርቃል፤
እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ
ዕብራይስጡ ወንዙ ይላል።
ላይ ይዘረጋል፤
ሰባት ታናናሽ ጅረትም አድርጎ
ይለያየዋል፤
ስለዚህ ሰዎች ከነጫማቸው መሻገር ይችላሉ።
16እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ
እንደ ሆነው ሁሉ፣
ከአሦር ለተረፈው ቅሬታ ሕዝብ፣
እንዲሁ ጐዳና ይዘጋጅለታል።
Copyright information for AmhNASV